By: የየበ ሸነን
ይሄ ነው አደገኛው ጨዋታ፤ ኅጎስ አስኪለማ አስር ኦሮሞ ይድማ የሚለው። በግልጽ አማርኛ ቶላ ከነቤተሰቦቹ (ማለትም ከነሚስቱ አያቱና ስድስት ልጆቹ) ለኅጎስ ብልጽግና መሬቱንና ንብረቱን አስረክቦ እንደ ኅጎስ ፍቃድ፤ ወይ የሱ አሽከር፤ አሊያም ለኅጎስ ስሜት ካልሰጠው የመንገድ ዳር ለማኝ እንዲሆን የሚወሰንበት። የዚህ አደገኛ የፖለቲካ ቁማር ማሳመኛ፤ “ኅጎስ ታግሎ በየአደባባዩ ተሰቅለ በውርደት ከምትረሸንበት የደርግ ስርአት ነጻ ስላወጣክ ነው” የሚል ነው። ለዚህም ሲባል ንብረትህን የመውሰድ ብቻ ስይሆን ህይወትህንም ተኩሶ የማጥፋት ባለሙሉ መብት ሆኗል። ይሆ እንግዲህ ተጽፎ የተቀመጠ ደንብና ህግ ባይሆንም ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ተግባራዊ ሲደረግ የከረመ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ወረቀት ላይ ያልሰፈረውን “ነጻ አውጥቶ የመዝረፍና የመግድል” መብታቸውን ተጠቅመው ለዝርፊያው እንዲያመቻቸው እነ ጃተኒ አሊን፤ ደራራ ከፈኒን፤ ነዲ ገመዳን፤ ኤቢሳ አዱኛን፤ ሙሊስ አባ ገዳን፤ ጉተማ ሀዋስን፤ ሼክ ሙሃመድ ሰኢዶን፤ ዮሴፍ ገመቹን፤ ኢንጅነር ተስፋውን ጨመዳን፤ ጋዲሳ ሂርጳሳ፤ ጃገማ በዳኔን፤ —እያለን በወያኔ የተገደሉ መቶ ሺህ ኦሮሞዎችን መዘርዘር እንቸላለን። የአኖሌንና ጨለንቆን ጭፍጨፋዎችን እንደ ማንረሳቸው ሁሉ፤ በወተር(1984)፤ በሲሬ(1985)፤ በሜታ ሮቢ(1988)፤ በዋቤ-ባሌ(1985)፤በአርበ ጉጉ፤ በበደኖ፤ በደደሳ፤ መንዲ፤ ባቢች፤ ስቻዎ፤ በተደጋጋሚ በባሌና ቦረና፤ በአንቦ፤በሻምቡ፤ በኮፈሌ፤
በ#OromoProtests 2014-2016 —እያልን የወያኔ ጭፍጨፋ ታሪኮችን መዝግበን የስቀመጥን መሆኑ ነው። የዚህ ሁሉ እብሪት መነሻና ማሳረግያ ኩሩ ኦሮሞ የመሆን ወንጀል ነው።
ኦሮሞ ስለሆንን ብቻ በመቶ ሺዎች ታስረናል። የአመለካከት ልዩነት ስላንጸባረቅን በገፍ ተገድልናል። የአመለካከት ልዩነት ማለት ደግሞ ጦርነት አይደልም። ስለ መብታችን መከበር ስለጠየቅን ብቻ ጦርነትን ተውጆብናል፤ ክብራችንን የሚነኩ ቅጥ ያጡ ማስፈራሪያይዎችና ዛቻዎች በባለግዜው ፀረኦሮሞ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ደርሰውብናል። አሁንም እየተከናወነ ያለ ነው። ይባስ ብለው በአኗኗሩም በታሪኩም ሆነ በባህሉ ጠባብ ሆኖ የማያውቀውን ታላቁን የኦሮሞ ህዝብ በተደጋጋሚ “ጠባብ” ብለው ስድበውታል።
ይታያቹ እንግዲ! ጓዙን ሸክፎ መጥቶ ለሀያ አምስት አመታት ያለመቋረጥ ሲዘርፍና ሲግድል ከሮሞ፤ በተፋጠነ መልኩ ለመዝረፍና ለመግደል እቅድ አውጥቶ ሲያበቃ። ግድያው ይቁም ዝርፊያውን ተውትና ካለኝ ንብረት ተከፍላቹ መኖር ትችላላቹሁ የሚለውን ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ “ጠባብ” ብሎ ለማሸማቃቅ የሚጣጣር በለግዜው ትምከትኛ– ወያኔ ሐርነት ትግራይ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገንዘቦችን ዘርፈው በተለያዩ የአውሮፓ ባንኮች አከማችተው፤ መቕለ ያለ አስኪመስልህ በተላያዪ የአዲስ አበባ ሰፈሮች ሌላውን መንጥረው በወል ሰፍረውበት፤ በህገወጥ መንገድ ግብር ሳይክፍሉበት ነግደው – ሌላውን ከሚያገኘው ግቢ አንድ አራተኛውን ለግብር እንዲክፍል አድርገው – ነጋዴውን አክስረው ከገቢያ አውጥተው፤ በኢንቬስትመንት ስም የገበሬውን መሬት ዘርፈው ከነልጆቹ መንገድ ዳር አውጥተው ጥለው፤ ለአይን የልተመቻቸውን አስረው ቶርች አርገው፤ ሌላው ለመብቱ መከበር ሰለጠየቀ ተኩሰው ገድልዉ፤ ይሄን ግልጽ የወጣ ዘረኝነት በመናገራህ ብቻ ዘረኛ፤ ጠባብ፤ ኦነግ፤ ጋኔል እያሉ ድግመው ዘረኝነታቸውንና ጥበታቸውን ይመሰክሩልሃ።
እኛም እንላቹሃለን:-
የኦሮሞ ህዝብ ፖለቲካ ከዘረኝነት የፀዳ ነው። ኦሮሞ ከዘሩ ብቻ በመነሳት የሚጠለው ህዝብ የለም። ሊኖርም አይችለም። በዘረኝነት ከክልሌ ውጥ ፤ ከዘሬ ጋር አትጋባ ፤አትቅረበው፤ አትገናኘው የሚለው አንዳች ወገን የለም። በዘር ንጽህናና የበላይንት ከቶም ቢሆን አይምንም። አንዲህ ካሉ ግብዝነትና የሞራል ዝቅተኝነት ጋር አይተዋወቅም። የግዜ ጉዳይ ሆኖ ነው እንጂ ሙሉ መብቱንና ንብረቱን የምያስመልስ ኩሩ ህዝብ ነው። በደሙ ኦሮሚያ ትለመልማለች እንጂ እሱ እየደማ አንተ አትለማም።
በኦሮሞ ደም ፤ ኦሮሚያ ትለምልም!!! የየበ ሸነን
__________________
Our contributor Yayyaba Shanan can be reached on his Facebook account at Lallaba Shanan. All views of the article is that of the writer. Xalayaa.com does not take full liability of the article. The author (Yayyaba Shanan) will take direct and indirect liability, and is fully responsible for the piece.